ደጆችሽ አይዘጉ መንፈሳዊ የአገልግሎት ማህበር

አመሰራረት ማህበሩ በሐምሌ 19 1998 ዓ.ም. በጅማ ሀገረ ስብከት በሰኮሩ ወረዳ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ደንብና ስርዓት መሰረት በናትሪ ደብረ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ተጉዘው በነበሩ ምዕመናን በጅማ ሀገረ ስብከት ፈቃድ ሰጭነት ተመሰረተ።

በጅማ ሀገረ ስብከት የገጠር አብያተ ክርስቲያናት ዛሬ ላይ ያሉበት ሁኔታ

በ2001 ዓ.ም. በጅማ ሀ/ስብከት ከነበሩት 283 አብያተ ክርስቲያናት 142 የተዘጉ ነበሩ። በአሁኑ ሰዓት 386 አብያተ ክርቲያናት የሚገኙ ሲሆን ከ2001 ዓ.ም ወዲህ ብቻ 103 አዳዲስ አብያተ ክርሰቲያናት ተሰርተዋል። በአሁኑ ሰዓት የተዘጉ አበያተ ክርስቲያናት ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ እንዲቀንስ ብዙ ጥረት ተደርጓል።

ስለ ማህበሩ

አመሰራረት ማህበሩ በሐምሌ 19 1998 ዓ.ም. በጅማ ሀገረ ስብከት በሰኮሩ ወረዳ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ደንብና ስርዓት መሰረት በናትሪ ደብረ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ተጉዘው በነበሩ ምዕመናን በጅማ ሀገረ ስብከት ፈቃድ ሰጭነት ተመሰረተ። ይህ ማህበር ተዘግቶ የነበረውን የናትሪ ደ/ሰ/ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ህንፃ አጠናቆ በሐምሌ 19 2000 ዓ.ም. ካስመረቀ በኃላ በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ዻዻስ በቀረበለት ጥሪ መሰረት በጅማ በአቅም ማጣት ምክንያት ተዘግተው የነበሩትን 139 አብያተ ክርስቲያናት ለማስገልገል ቆርጦ ተነሳ። በመቀጠል ይህንን ሰፊ አገልግሎት ለማከናወን የስምና አቋም ማሻሻያ በማድረግ በነሐሴ 2000 ዓ.ም. ደጆችሽ አይዘጉ መንፈሳዊ የአገልግሎት ማህበር ተብሎ እንዲጠራ የሀገረ ስብከቱ እና የጠቅላላ ጉባኤ አዎንታ በማግኘት ስራውን ቀጥሏል።

ቤተክርስቲያን

በ1901 ዓ.ም የተገነባዉ የ ላፍቲ ኪደነምህረት ቤተክርስቲያን::ይህ በዙሪያው ከ100 በላይ አባወራዎች የነበሩበት ሲሆን ዛሬ ላይ ይህ ደብር ተዘግቶ አገልግሎት መስጠት ካቆመ ፪ አመት እንዳለፈው የነበረውን ምዕመን ተኩላ አየወሠደው አሁን የቀረው አባወራ ወደ 60 አሽቆልቁሏል፡፡
በጅማ ሃገረ ስብከት በጮራ ቦተር ወረዳ ካራ ቅዱስ ሚካኤል በደብሩ ያሉት ምዕመናን በቁጥር ፮ ቢሆኑም ጠንካራና ለቤተክርስቲያን ቀናኢ በመሆናቸው በአጭር ጊዜ የጀመሩት ቤተክርስቲያን እንዲህ ባማረ መልኩ አጋምሰዋል እናም ይሄን የምናይ ምዕመናን የአቅማችንን በማድረግ ለፍፃሜ ብናበቃላቸው በእግዚአብሔር ስም ጥሪዬን አቀርባለሁ ፡፡

የናቡቴ ቁ. ፪ ስራው ሲጠናቀቅ የሚኖረው ገጽታ.

የገበያ ማዕከል ግንባታው ሲጠናቀቅ በጅማ ሀገረ ስብከት የሚገኙ የተቸገሩ የገጠር አብያተ ክርስቲያናት ድጎማ በማድረግ የሚኖረው አስተዋፆ እጅግ ከፍተኛ ነው። በዚህም በትንሹ ከ100 በላይ የገጠር አብያተ ክርስቲያናት እና የስብከተ ወንጌል ተቋሙ  ይደገፉበታል።