ስለ ማህበሩ

አመሰራረት ማህበሩ በሐምሌ 19 1998 ዓ.ም. በጅማ ሀገረ ስብከት በሰኮሩ ወረዳ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ደንብና ስርዓት መሰረት በናትሪ ደብረ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ተጉዘው በነበሩ ምዕመናን በጅማ ሀገረ ስብከት ፈቃድ ሰጭነት ተመሰረተ። ይህ ማህበር ተዘግቶ የነበረውን የናትሪ ደ/ሰ/ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ህንፃ አጠናቆ በሐምሌ 19 2000 ዓ.ም. ካስመረቀ በኃላ በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ዻዻስ በቀረበለት ጥሪ መሰረት በጅማ በአቅም ማጣት ምክንያት ተዘግተው የነበሩትን 139 አብያተ ክርስቲያናት ለማስገልገል ቆርጦ ተነሳ። በመቀጠል ይህንን ሰፊ አገልግሎት ለማከናወን የስምና አቋም ማሻሻያ በማድረግ በነሐሴ 2000 ዓ.ም. ደጆችሽ አይዘጉ መንፈሳዊ የአገልግሎት ማህበር ተብሎ እንዲጠራ የሀገረ ስብከቱ እና የጠቅላላ ጉባኤ አዎንታ በማግኘት ስራውን ቀጥሏል።