ናቡቴ ቁጥር-1

ግብረ ናቡቴ ቁጥር-1: የንብ ማነብ ፕሮጀክት የያዘ ሲሆን ይህንኑ ፕሮጀክት ቀደም ሲል በየቡ ቅ/ሚካኤል እና በናትሪ ደ/ሰ/ቅ/ገብኤል ቤ/ክ አምሳ አምሳ የንብ ቀፎ በማስቀመጥ ስራው ሲካሄድ ቆይቷል።ነገር ግን የበለጠ ምርታማ ሆኖ ለመገኘት ይህንኑ ፕሮጀክት በተመረጡ 20 ደብራት ላይ ተግባራዊ ቢደረግ አሁን እየታየ ካለው ውጤት የተሻለ ሊሆን እንደሚችል ከባለሞያ በመጣው የመስክ ጥናት ሊረጋገጥ ችሏል። ስለሆነም የማህበሩ አመራር በተሰጠው ሞያዊ አስተያየት መሰረት ከነሐሴ 2007 ዓ.ም. ጀምሮ በጅማ ሀ/ስ በገጠር ካሉ አብያተ ክርስቲያናት መካከል ለዚህ ስራ በተፈጥሮዊ አቀማመጣቸው አመቺነታቸው የተለዩ 20 ደብራት ላይ ምርጫ በማካሄድ አስፈላጊውን በቂ ስልጠና ደረጃ በደረጃ እንዲሰጣቸው በማድረግ እና ለስራው የሚያስፈልጉ ቁሳቁስ በመለገስ ስራው በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል። የንብ ማነብ ስራው ምርት እስከሚሰጥበት ጊዜ ድረስ በከፍተኛ ባለሞያዎች ደረጃ ክትትል የሚደረግበት ይሆናል። በስተመጨረሻ ለየደብራቱ ርክክብ በማካሄድ ከልማት የሚጠቀሙበት ሁኔታ ይመቻችላቸዋል።