ናቡቴ ቁጥር-2

ግብረ ናቡቴ ቁጥር-2: በጅማ ከተማ ውስጥ የባለ አራት ፎቅ ሁለገብ የገበያ ማዕከል የመገንባት ሀሳብ የያዘ ፕሮጀክት ሲሆን የዲዛይን እና የአፈር ምርመራ ውጤት በሙሉ በማጠናቀቅ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ከጅማ ሀገረ ስብከት ጋር በመሆን የግንባታ ፈቃድ ለማውጣት ጥረት እየተደረገ ይገኛል። ቀደም ሲል ማህበሩ ህንፃው ሊሰራ የታሰበበትን መሬት ከአንድ ክርስቲያን ግለሰብ ጋር በመደራደር በብር 750,000.00/ ሰባት መቶ አምሳ ሺ ብር/ የተገዛ ሲሆን ስፍራው የ2000 ካ.ሜ. ስፋት ያለው ነው ። ይህ ህንፃ በአጭር ጊዜ ተገንብቶ ለኪራይ መብቃት ቢችል በጅማ ገጠር ያሉ አብያተ ክርስቲያናት በጀት በመሸፈን ጉልህ ድርሻ ይኖረዋል።