ናቡቴ ቁጥር-3

ግብረ ናቡቴ ቁጥር-3 : ይህ ፕሮጀክት በጅማ ሀገረ ስብከት በሊሙ ወረዳ በአቡካኮ ባለወልድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚካሄድ የቡና ልማት ሲሆን ይህንን ልማት በ25 ሄክታር ቦታ ላይ ከ 77ሺ በላይ የቡና ችግኝ በማፍላት 22 ሄክታር መሬት ለማልማት ተችሏል። ይህንን ፕሮጀክት ከበላይ ሆነው እንዲከታተሉት በአዲስ አበባ እና በጅማ ተናቦ የሚሰራ ኮሚቴ የተዋቀረለት ሲሆን በሳይቱ ላይ በቋሚነት ፐሮጀክቱን የሚከታተል በቡና ክትትል ላይ ከፍተኛ ልምድ ያለው ባለሞያ በስራ አስኪያጅ የስራ መደብ እንዲቀጠር ተደርጓል። በባለፈው አመታት የተተከሉ ችግኞች መካከል 70% በላይ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ከፕሮጀክቱ ክትትል ለመረዳት ተችሏል። ይህ ፕሮጀክት በአጠቃላይ በደብሩ ባለው ቦታ ሙሉ ለሙሉ ተሸፍኖ መሰራት የሚቻልበትን እቅድ በመያዝ እና ተግባራዊ በማድረግ ከልማቱ የብዙ ገጠር አብያተ ክርስቲያናት ችግር በመቅረፍ በቋሚነት የመተዳደሪያ ገቢ ምንጭ ሊፈጥርላችው እንደሚችል አሁን በፕሮጀክቱ ላይ የሚታየው ውጤት ያሳያል።