ግብረ ሎዛ

በመፅሐፍ ቅዱስ በዘፍ. 28 ፥ 19 እንደተገለፀው ቅዱስ ያዕቆብ የአባት እናቱ ቃል ሰምቶ ሎዛ ወድምትባል ስፍራ ሄደ ፣በዚያም ፀሐይ ጠልቃ ነበር እና ከዚያ አደረ በዚያም ስፍራ ድንጋይ አነሳ ከራሱም በታች ተንተርሶ ተኛ፣ የሚያስደንቅ ሕልምም አለመ። ያዕቆብም ማልዶ ተነሳ ተንተርሶበት የነበረውንም ድንጋይ ወስዶ ሐውልት አድርጎ አቆመው በላዩም ዘይትን አፈሰሰበት ያንን ስፍራ ቤቴል ብሎ ጠራው ። ያዕቆብ በሎዛ ለቤተ እግዚአብሔር የአቅሙን አድርጎ ያንን ቦታ እንዳቀናው ሁሉ፣ እኛም በዚህ ዘመን የምንገኝ ክርስቲያኖች የድርሻችንን በመወጣት በተለያየ ችግር ምክንያት ተዘግታ የምትገኝ የገጠር ቤተ ክርስቲያንን በአቅማችን መርዳት ይጠበቅብናል። ስለሆነም ይህ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮጀክት ለሀገር ውስጥ አንድ ብር በውጭ ለሚገኙ አንድ ዶላር የምንሰጥበትን አሰራር በተደራጀ አካሄድ የሚሰራ ሲሆን ፣ይህንን የገቢ ማሰባሰቢያ ዘዴ በሁሉም አካባቢ በተለይም በመስራያ ቤት በመኖርያ ቤት፣ በንግድ ስፍራ፣ በመዝናኛ ስፍራዎች በትምህርት ቤት እንዲሁም በልዩ ልዩ ማህበራት በቡድን ተደራጅተው ለሚመጡ ሁሉ በቀላሉ ገቢ የሚያሰባስቡበት መንገድ ያመቻቻል። በአጠቃላይ በፕሮጀክቱ ውስጥ ድሃ ሀብታም፣ ወጣት ሽማግሌ፣ ሴት ወንድ ፣ገጠር ከተማ እንዲሁም በሀገር ውስጥ ከሀገር ውጪ ሳይል ሁሉንም እንደየአቅሙ ከበረከቱ የሚያሳትፍ የአንዲት ብር ለአንዲት የገጠር ቤተ ክርስቲያን በየወሩ የሚሰጥበት የልግስና ፕሮጀክት በመሆን ያገለግላል።