ግብረ ክርስቲያናዊ ቤተሰብ

ይህ ፕሮጀክት የቅዱስ ዻውሎስ መልዕክት መሰረት አድርጎ የተነሳ ሲሆን “ባንዝልም በጊዜው እናጭዳለንና መልካም ስራን ለመስራት አንታክት እንግዲያስ ጊዜ ካገኘን ዘንድ ለሰው ሁሉ ይልቁንም ለሃይማኖት ቤተ ሰዎች መልካም እናድርግ” ገላ6-10 ሲል በመከራቸው አምላካዊ ቃል መሰረት በማድረግ በጅማ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በማጣት በብዙ ጉዳት የደረሰባቸውን ምዕመናን ለመታደግ የተዘጉ አብያተ ክርስቲያናትነ ለማስከፈት ተብሎ የተወጠነ ፕሮጀክት ነው። ይህ ፕሮጀክት ጊዜያዊና ፋታ ሰጪ የሆነ እና ለሁለት አመታት የሚዘልቅ አገልግሎትን የሚያሰጥ ፕሮጀከት ነው። ምዕመናን በየወሩ ብር 800.00/ስምንት መቶ ብር ብቻ/ ለሶስት አገልጋዮች የሚሆን ወርኃዊ ደሞዝ በመቻል ቤተ ክርስቲያንን የሚስተዳድሩበት እንቅስቃሴ ነው። በዚህ ፕሮጀክት ማህበሩ በህዳር 27 2002 ዓ.ም. አዘጋጅቶት በነበረው ታላቁ የሚሊኒየም ጉበኤ በተገኘው ገቢ አብያተ ክርስቲያናቱን ከአንድ አመት በላይ ለሆነ ጊዜ በማስከፈት አገልግሎት እንዲሰጡ አስችሏል።