ታላቅ የበረከት ጥሪ!

በጅማ ሀገር ስብከት የ100 አብያተ ክርስቲያናት ችግር ይቀርፋል በሚል በጅማ ከተማ እየተገነባ ያለው ህንፃ በምድር ቤቱ ላይ ከመጋቢት ወር በኃላ በሚዘንበው የተፈጥሮ ዝናብ የሚያጋጥመውን ከፍተኛ የውሃ መጠራቀም አደጋ ለመቀነስ በርካታ ገንዘብ /እስከ 2 ሚሊዮን/የሚጠይቅ ስራ መሰራት ይገባዋል። ይህንን ችግር ከሳይቱ መሀንዲስ ለመረዳት ተችሏል።ስለሆነም ለዚህ ታሪካዊ ሕንፃ ቶሎ መጠናቀቅ እና ከፊታችን ያለውን የውሃ መጠራቀም አደጋ ለመቀነስ ማህበራችን ታላቅ የበረከት ጥሪ በዚህ የማህበራዊ ድህረ ገጽ ላለነው ምዕመናን ያቀርባል። በተለይ በሞባይል ባንኪግ ለሚጠቀሙ ከ100ብር ጀምሮ አስተዋፆ ብናደርግ የብዙ ገጠር አብያተክርስቲያናትን ተስፋ እናለመልማለን። ዛሬ ነገ አንበል ከበረከቱ እንሳተፍ። ሞባይል ባንኪግ የሌለን ሰዎች ሞባይል ባንኪግ በአቅራቢያችን ለሚጠቀሙት በካሽ በመስጠት እና ወደ ማህበሩ ሂሳብ ቁጥር እንዲልኩ በማስቻል ልግስናውን ቀልጣፋ ማድረግ ትችላላችሁ። ዋናው ነገር ከልብ መነሳሳት ነው። የማህበሩ ባንክ ቁጥር የኢት.ንግድ ባንክ 1000010794521

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *