Services
የናቡቴ ቁ.1
ከመጋቢት 2003 ዓ.ም. ጀምሮ 23 ለሚደርሱ ደብራት 200 ዘመናዊ ቀፎ አሰርቶ በመለገስ እና ከ60 በላይ ለሆኑ የደብራት ተወካዮች ስልጠና በመስጠት የተመረተውን ማር በማከፋፈል ብዙ ስራ ተሰርቷል።
ናቡቴ ቁ.2
ከ100 አብያተ ክርስቲያናት በላይ እና የስብከተ ወንጌል ተቋሙን በቋሚነት ለማስገልገል በጅማ ከተማ እየተገነባ የሚገኘው ሁለገብ የባለ 4 ፎቅ ህንፃ 35% ስራው ተከናውኗል። እስከ አሁን ከ18 ሚሉዮን ብር በሊይ ወጪ የተደረገ ሲሆን ህንጻውን ለማጠናቀቅ እስከ 40 ሚሊዮን ብር ያስፈልገናል።
ናቡቴ ቁ.3
በሊሙ ኮሳ ወረዳ አቦካኮ ባለወልድ ቤ/ክ ውስጥ በ25 ሄክታር ላይ እየለማ የሚገኘው የቡና እርሻ በአማካኝ ከ 100 ኩንታል በላይ ቡና እየሰጠ ይገኛል። ከቡናው ሽያጭ በሚገኘው ገቢ የተዘጉ አብያተ ክርስቲያናት እየተከፈቱ ይገኛሉ።
ናቡቴ ቁ.4-
በ 5 ደብራት ላይ
የፍራፍሬ ልማት እና የባለሞያ
ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።
