ስለ ማህበሩ
ስለ ማህበሩ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
“ደጆችሽ አይዘጉ”መንፈሳዊ የአገልግሎት ማህበር በጅማ ሀገረ ስብከት በህጋዊ መንገድ በ1998 ዓ.ም. ተቋቋመ። ማህበሩ የተዘጉ 142 አብያተ ክርስቲያናትን አስከፍቷል ፣በጅማ ገጠር ውስጥ በ 22 ወረዳዎች ላይ በአካባቢው ቋንቋ የሚሰብኩ 44 ደቀመዛሙርት በማሰልጠን እና በማሰማራት ስብከተ ወንጌልን እንዲስፋፋ አድርጓል። እንዲሁም በጅማ እና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የሚያገለግል የሰባክያን ማሰልጠኛ ተቋም በ4ሚሊዮን ብር በመገንባት አስመርቆ ለስራ አብቅቷል፣ የገጠሯ ቤተ–ክርስቲያን በልማት እራሷን በማስቻል ከልመና የምትላቀቅበትን የልማት ፕሮጀክት በመንደፍ በፍራፍሬ ልማት፣ በንብ ማነብ፣ በቡና ልማት እና በወፍጮ ስራ ከ30 ደብራት በላይ ከሚገኘው ገቢ እንዲጠቀሙ እየተደረገ ይገኛል። በአሁኑ ሰዓት የማህበሩ ትልቁ ልማት በጅማ ከተማ እየተገነባ የሚገኘው ሁለገብ ህንጻ ሲሆን ይህንን ህንፃ ከፍፃሜ ለማድረስ በጥቅሉ ከ40 ሚሊዮን ብር በላይ ያስፈልጋል። ይህ ሰነድ የተዘጋጀው ምዕመናን ይህንን በጎ ጅምር በማየት የሚቻላቸውን አስተዋፆ እንዲያደርጉልን ለማበረታታት ነው።
ግብረ ሎዛ
አንድ ሰዉ አንድ ብር ለአንድ ቤተ ክርስቲያን በወር የሚሰጥበት የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮጅክት
ግብረ መዝገበ ሰማይ
በቋሚ ትዕዛዝ ከተቀማጭ የባንክ ሂሳብ ላይ ፍቃደኛ ከሆነዉ ሰዉ ተቆርጦ ወደ ማህበሩ አካዉንት ገቢ የሚደረግበት የገቢ ማሰባሰቢ ፕሮጅክት፡፡
ግብረ ጥበበ ባስልኤል
ሰዎች በሞያቸው አገልግሎት የሚሰጡበት ስልት
ግብረ ትሩፋተ ወንጌል
የባላ 500 እና 1000 ብር የበረከት ሰርተፍኬት ሽያጭ
ልዩ ልዩ አገልግሎቶች