የስብከተ ወንጌል ማስፋፍያ - ፕሮጀክት ኤርጋሞታ
በሐምሌ 18 2002 ዓ.ም
በሐምሌ 18/2002 ዓ.ም ኤርጋሞታ የተሰኘው የሰባክያን ወንጌል ማሰልጠኛ ተቋም በ250000 ብር ወጭ በማድረግ የጭቃ ቤት በመስራት በብጹዕ አቡነ እስጢፋኖስ ተመርቆ 22 የሰባኪያን ወንጌል ተቀብሎ ማሰልጠን ተጀመረ፡፡
ከሐምሌ 2003 ዓ.ም - ታህሳስ 2005 ዓ.ም
ሁለት ዓመታት 44 ሰባክያን ወንጌል በሁለት ዙር በማሰልጠን ወደ ሁሉም ወረዳዎች እንዲመደቡ ተደረጉ፡፡
በዚህም በጠቅላላ እስከ 1 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጓል።
በጥር 25 2006 ዓ.ም
በጥር 25/2006 ዓ.ም ለጅማ እና ለምዕራብ ኢትዮጵያ የሚያገለግል ዘመናዊ የስብከተ ወንጌል ማሰልጠኛ ተቋም በ4
ሚሊዮን ብር ተገንብቶ በመጠናቀቁ በቅዱስ ፓትርያርኩ ተባርኮ ተመረቀ፡፡
በሐምሌ 2009 ዓ.ም
ሶስተኛውን ዙር ስልጠና በሐምሌ 2005 ዓ.ም ተጨማሪ 26 ሰባክያነ ወንጌል ተመርቀዉ ወደ ወረዳዎች ተመደቡ።
ከ2005 ዓ.ም. ጀምሮ
ሰባክያነ ወንጌሎቹ ተመድበዉ ከሚያገለግሉባቸዉ ወረዳዎች ዉስጥ በ 12 ወረዳዎች በተደረገ ስብከተ ወንጌል እንቅስቃሴ ብቻ 278 ቤተሰቦች እና 4 ፓስተሮች ተመልሰዋል ። ከዚያም በኃላ ባለት ተከታታይ ዓመታት በሺ የሚቆጠሩ ምዕመናን ከሌልች እምነት ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለመመለስ ተችሏል።
ሰባክያነ ወንጌሎቹ በገጠር ተንቀሳቅሰው ስብከተ ወንጌል ለማቀላጠፍ እንዲረዳቸው 3 አዳዲስ ሞተር
ሳይክሎችን ገዝተን ለሶስት ወረዲዎች ሰጥተናል።
